
በዓለምአቀፉ የዐማራ ማህበራት ሕብረት አስተባባሪነት በኢትዮጵያ በብሄር ማንነት ምክንያት የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም “የአማራ እናት እንባ” በሚል መሪ ቃል ታሪካዊ ዘመቻ ተካሄደ።
በተለያዩ የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች ለአንድ ወር በቆየው የተቀናጀ ሰልፍ ፥ ተሳታፊዎች ፥ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ከአማራ ህዝብ ጎን እንዲቆም እና በአብይ አህመድ ዘር ጨፍጫፊ መንግስት ላይ ማዕቀብ እንዲጣልም ጠይቀዋል!
እ.አ.አ ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 27 ፣ 2025 ዓ.ም ድረስ ፥ የአለም አቀፉ የአማራ ማህበራት ህብረት እና በየሀገሩ የሚገኙት አጋሮቹ “የአማራ እናት እምባ” በሚል መሪ ቃል የተቀናጀ የተቃውሞ ሰልፍ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ስምንት ዋና ዋና ከተሞች ለ32 ቀናት አካሂደዋል።
- ለንደን፣ ዩናይትድ ኪንግደም – ጥቅምት 26
- ፍራንክፈርት፣ ጀርመን – ህዳር 8
- ሄግ፣ ኔዘርላንድስ – ህዳር 12
- ሚኒያፖሊስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ – ህዳር 16
- ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ – ህዳር 21
- ሳንዲያጎ፣ አሜሪካ – ህዳር 23
- በርሊን፣ ጀርመን – ህዳር 26
- ብራስልስ፣ ቤልጂየም – ህዳር 27
ይህ ዘመቻ በኢትዮጵያየ አማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ብሔር ተኮር ጥቃት በዓለም አቀፍ ማህብረሰብ እውቅና እንዲያገኝ እና ጣልቃ ገብተው አፋጣኝ የሰብአዊ እርዳታ መስጠት እንዲችሉ ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
የዘመቻው ዋና አላማ ፥ በቀጥታ ወደ ዓለም አቀፍ መንግስታት እና የፍትህ ተቋማት ያነጣጠረ ሲሆን፤ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ብሄር ተኮር የዘር ማጥፋት ፖሊሲ ስለያዘ ፥ ሰላማዊ ዜጎችን ከጥፋት መታደግ የሚል መልእክትም አዝሏል። የተቃውሞ ተሳታፊዎችም ፥ ይህን የዘር ጭፍጨፋ ማስቆም እስኪቻል ድረስ በተለይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል እና የንግድ ግንኙነቱ እንዲቋረጡ ጭምር ጠይቀዋል። ዘመቻው በጦር ወንጀሎች እና ወንጀለኞች ላይ የተባበሩት መንግስታት እና የአውሮፓ ህብረት መደበኛ ምርመራዎችን እንዲያደርግ እና የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የ2019 ዓ.ም የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲሰርዝም ጠይቀዋል።
የለንደን ሰልፍ፡ መክፈቻ
በጥቅምት 26፣ 2025 ዓ.ም በለንደን የተካሄደው የመክፈቻ ሰልፍ የ “አማራ እናቶች እንባ” ዘመቻን መሰረት አስቀምጧል። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ባደረጉት የአማራ ማህበራት ጥምረት በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በኦክስፎርድ ሰርከስ ተገኝተው ወደ ትራፋልጋር አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ተሰብሳቢዎቹ በዋናነት ሀዘንን ለማመልከት ይረዳ ዘንድ ጥቁር ልብስ ለብሰው “አማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው የዘር ማጥፋት ይቁም” የሚሉ መልእክቶችን አስተላልፈዋል።
ወደ ማምሻው አካባቢ ዝግጅቱ ወደ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ተሸጋግሮ በዘር ጭፍጨፋው የተገደሉትን ሰላማዊ ዜጎች፣ ሕጻናት እና ሰማዕታት ለማሰብ የህሊና ጸሎት ተደርጓል። አንድ የዝግጅቱ ተካፋይ በስሜት ተሞልቶ ለተሰበሰበው ሕዝብ፣
“በገዛ አገራቸው ለተገደሉት፣ ለተፈናቀሉት እና ለተጨፈጨፉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አማሮች እንዲሁም ድምፅ ለተነፈጉ ንጹሁን ሰዎች ድምፅ ለመሆን እዚህ ተሰባስበናል…” ሲል ተናግሯል።
የፍራንክፈርት ሰልፍ፡ የሰብአዊ ቀውስ ውስጥ እንደሆንን አለም ይወቅልን!
እ.ኤ.አ በ ህዳር 8 ፣ 2025 ዓ.ም በፍራንክፈርት የተደረገው ሰልፍ ሰብአዊ መብት ቀውስ ላይ ትኩረት በማድረግ ለአካባቢው ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል ። ተሰብሳቢዎቹም በጀርመን እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ መፈክሮች በማሰማት አፋጣኝ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ጣልቃ ገብነት እና በዘር ጭፍጨፋው ምክንያት የተፈጠረውን የጅምላ መፈናቀል አደጋ ለመከላከል እንዲቻል አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ይህ የድጋፍ ሰልፍ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የተካሄደውን ሰፊ የተቀናጀ የአማራ ዲያስፖራዎችን ንቅናቄ አጉልቶ የሚያሳይ ነው።
የሄግ ሰልፍ፡ የፍትህ ጥሪ
እ.አ.አ ህዳር 12 ፣ 2025 ዓ.ም በከተማው ባቡር ጣቢያ አቅራቢያ የተደረገው እና በኔዘርላንድስ በሚገኘው የአማራ ማህበር አዘጋጅነት የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ለአለም አቀፍ የፍትህ ተቋማት ቀጥተኛ ጥሪ ጥልቅ ተምሳሌታዊ ፋይዳ ነበረው።
አዘጋጆቹ የአማራ ህዝብ በአሁኑ ሰአት የገጠመውን የህልውና አደጋ በተመለከተ ማብራሪያዎችን አቅርበዉ ለኔዘርላንድ ነዋሪዎች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲህ ብለውም አስረድተውም ነበር፥
“የአማራ ህዝብ በማንነቱ፣ በብሄሩ እና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታይነቱ እየተገደለ ነው፣ ነፍሰ ጡር እናቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ህጻናት አማራ በመሆናቸው ብቻ ተደፍረዋል፣ ተሰቃይተዋል፣ ወጣቱ ትውልድም ከትውልድ አገሩ በግፍ የዘር ማጽዳት እየተደረገበት ነው“
በተጨማሪም ተቃዋሚዎች የኔዘርላንድ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የኢኮኖሚ ንግድ እንዲያቆም ጠይቀው ይህንንም የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኔዘርላንድ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማቅረብ ቃል ገብተዋል። ጎን ለጎንም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሳተፉትን ሰዎች በህግ እንዲጠየቁ የአለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።
የበርሊን ሰልፍ፡ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ የሚደርሰው ግድያ እና መሳደድ በአስቸኳይ እንዲቆም የሚጠይቅ ነበር።
ህዳር 26 ፣ 2025 ዓ.ም በበርሊን የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን በማውገዝ የዘመቻውን አድማስ አስፍቷል። ተቃዋሚዎች በኦሮሚያ ክልል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ የተፈጸሙ ተደጋጋሚ ግድያዎችን አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በዝምታ ማየታቸው በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም የአለም ማህበረሰብ ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲያደርግ ሰልፉ አሳስቧል።
የሚዲያ ተሳትፎ እና የዘመቻዎቹ ጠቀሜታ
የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች አብይ አህመድ በሰው አልባ አውሮፕላን በመጠቀም በኢትዮጵያ ያልታጠቁ ሲቪል ሰዎች ላይ የሚያደርሰውን የዘር ማጽዳት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሁን ዜጎችን መፈናቀል እና እንደ ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች ባሉ ወሳኝ መሰረተ ልማቶች ላይ የደረሱትን ውድመቶች ጨምሮ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሪፖርት አድርገዋል።
በተያያዘም “የአማራ እናት እምባ” በሚል የተዘጋጁት ሰልፎች እንደ ሮይተርስ ኮኔክት ባሉ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን ያገኙ ሲሆን በተለያዩ ቋንቋዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ሰፊ ዘገባዎች በመሰራታቸው የአለምአቀፍን የሚዲያ ትኩረትን አግኝተዋል።
የተቃውሞ ትእይንቶቹ ግዝፈት የዲያስፖራ ማህበረሰቡን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የሚመለከታቸው ዜጎችን ሰፊ ተሳትፎ ያሳያል። እንዲሁም የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለዝግጅቶቹ መሳካት ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኖቤል ሽልማትንም እንዲነጠቅ ከመገዳደርም ጋር ተዳምሮ ዲያስፖራው ለአማራ ህዝብ እውነትን፣ ፍትህን እና ሰብአዊ መብትን ለመጠየቅ ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት አሳይቷል።
ስለ ዘመቻው
“የአማራ እናት እንባ” ዘመቻ የአማራን ዘር መጥፋት እና ሰብአዊ መብት ቀውስ ለመቅረፍ እስከ ዛሬ የተደረገውን እጅግ ሰፊ የተቀናጀ አለም አቀፍ የድጋፍ ጥረትን አስቀጥሏል። በተለያዩ አህጉራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከአማራ ህዝብ ጎን እንዲቆም እና ለንጹሃን ህዝቦች ጥበቃ እንዲጠይቁ አሳስቦ ተጠናቋል።

