Skip to content

Vereniging van Amharas in Nederland (VAN)

የአማራ ማኅበር በኔዘርላንድ

ድምጽ ለተነፈጉ ድምጽ እንሁን!

Let us be the voice for the voiceless!

መቅድም

የአማራ ማሕበር በኔዘርላንድ የኔዘርላንድ አገረ-መንግሥትን ሕግና ደንብ ጠብቆ በማሕበሩ አባላት ፍቃደኝነት እና ስምምነት በይፋ የተቋቋመ ሕዝባዊ ማሕበር (Civic Association) ነው። በተለያዩ ምክንያቶች ከአገር ቤት ለቀው እንዲሁም በኔዘርላንድ ተወልደው የሚኖሩ የአማራው ማሕበረሰብ በሚኖሩበት የኔዘርላንድ አገር ውስጥ ጠቃሚ ባህላቸውን እና ልምዶቻቸውን በፆታ፣ በዕምነት፣ በዕድሜ እና በፖለቲካ አመለካከት ላይ ልዩነት ሳያደርጉ በወንድምማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ ተሰባስበው ሳይለያዩ እርስ በርስ በመተሳሰብ የጋራ አቅማቸውን በማጎልበት ለመረዳዳት፣ በማንነትን ባህልን፣ የግል እና የገራ አቅምና ክህሎቶችን ለማዳበር ታስቦ የተመሠረተ ነው።

Latest News

በጠቅላላው በሪፖርቱ ውስጥ በስም ከተዘረዘሩት ብቻ  450 በላይ ንጹሃን ዜጎች  ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ብዙዎቹ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ህጻናት ጭምር ናቸው። ከተጎጂዎቹ መካከል ገና 15 እና 16 ዓመት የሞላቸው ወጣቶች፣ እንዲሁም ከ4 አመት እድሜ ጀምሮ ያሉ ህጻናት ይገኙበታል።ሪፖርቱ ካካተታቸው ምስክርነቶች መካከል የአንድ ቤተሰብ አባል የተናገረችው ይገኝበታል። ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ላይ የታጠቁ ኃይሎች ቤቷን ከበው አባቷን፣ ሁለት አጎቶቿን እና የአጎቷን ልጅ ወሰዱ። ሴቶችና ህጻናት ተትተው ወንዶች ብቻ ተወሰዱ። የተኩስ ድምጽ ሲሰሙ የቀሩት ቤተሰቦች ወደ ጫካ ተበታተኑ። በዚያች ሌሊት የአጎቷና የአጎቷ ልጅ አስከሬን ተገኘ። ቀሪዎቹ በህይወት እንዳሉ በስልክ ተነግሯቸው፣ ቀጥሎም 1,000,000 ብር ካሳ እንዲከፈል ተጠየቁ። ቤተሰቡ 750,000 ብር ሰብስቦ ቢያስረክብም፣ ከቀናት በኋላ የተያዙት ሰዎች አስከሬን በሌላ ወረዳ ተጣለ ተብሎ ተነገራቸው። ይህ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ብቻ ሲሆን፣ በሪፖርቱ ውስጥ ተመሳሳይ ስቃይ ያሳለፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ስም ዝርዝር ተመዝግቧል።

ኢትዮጵያዊው ምሁር፣ ደራሲ እና የንጉሣዊ ቤተሰብ ተወላጅ የሆኑት ልዑል አስፋወሰን አሰራተ ካሳ በአውሮፓ ፓርላማ ፊት ባደረጉት ጠንካራ ንግግር፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ፣ በተለይም በአማራ ህዝብ እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያን ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ባለው እና በስፋት በማይዘገበው ጥልቅ አደጋ ላይ ያላቸውን ዝምታ እንዲሰብሩ አሳስበዋል።ልዑል አስፋወሰን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት፣ የያዚዲ የዘር ማጥፋት እና የስሬብሬኒካ ጭፍጨፋን ታሪክ በማስታወስ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እጁን አጣጥፎ በመቀመጥ ቆይቶ በኋላ ላይ ጸጸቱን የገለጸባቸውን ወቅቶች አውስተዋል። ጸጸት ፍትህ ፍትህ ሊያመጣ እንደማይችል በመሞገት፣ ዓለም በኢትዮጵያ ውስጥ ተመሳሳይ ስህተት እንዳይደግም ጥሪ አቅርበዋል።

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችና በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ሥርዓታዊ የዘር ማጥፋት፣ ጭፍጨፋ እና የቅዱሳት መካናት ውድመትን በጥብቅ የሚያወግዝ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በረጅም የታሪክ ዘመናት በእምነታዊ እሴቶቿ፣ በኪነ-ህንፃ፣ በስነ-ጥበብ፣ በስነ-ስዕል፣ በዜማ፣ በፊደል፣ በትምህርት፣ በስነ-ምግባርና በታሪክ ረገድ ለሀገሪቱ ህልውና የላቀና ወደር የሌለው ባለውለታ መሆኗ ይታወቃል። ከሁሉም በላይ ሀገራችን በወራሪ ኃይሎች ሳትደፈር ነፃነቷ ተጠብቆ ለትውልድ እንድትሻገር ህዝቡን በጀግንነትና በሀገር ፍቅር በማስተማር ረገድ ያደረገችው ተጋድሎና ያሳየችው አርአያነት ታሪክ የማይረሳው እውነት ነው።

History shows that genocide is rarely acknowledged while it is happening. Recognition usually comes later, after the graves have been counted and the survivors are too few to speak. The Amhara people are not waiting for a courtroom verdict. They are dying. The law says this is genocide. The framework says this is genocide. The world’s foremost genocide prevention experts say this is genocide. The survivors, those still alive to speak, are telling us this is genocide.

በተለያዩ የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች ለአንድ ወር በቆየው የተቀናጀ  ሰልፍ ፥ ተሳታፊዎች ፥ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ከአማራ ህዝብ ጎን እንዲቆም እና በአብይ አህመድ ዘር ጨፍጫፊ መንግስት ላይ ማዕቀብ እንዲጣልም ጠይቀዋል!

Upcoming Event! - Fundraising Campaign for Amhara Communities in Need!

From our past work...

A memorial for Amhara war victims & a members and supporters' meet-and-greet program in Amsterdam

July 2026

Global Protest "No ballot while bullets fly!" at Belgium, Brussels

May 2026

Protest Against the Genocidal Abiy Ahmed's Regime at The Hague Ministry of Foreign Affairs

March 2026

Protest Against the Ethiopian Government at The Hague

November 2025

AAN Meeting

2nd Annual Meeting of AAN in Amsterdam

October 2025

Candlelight in Memory of the Amhara Victims in Amsterdam Dam Square

May 2025

Peace Rally in Brussels, Belgium, Against the Amhara Genocide in Ethiopia

Humanitarian Work in Lasta Belbela Giorgis

Contact Us

We would love to hear from you.
Feel free to reach out using the below details.

Visit Us

Address:

Robijnstraat 12 2, 1074VE Amsterdam