የአማራ ማሕበር በኔዘርላንድ የኔዘርላንድ አገረ–መንግሥትን ሕግና ደንብ ጠብቆ በማሕበሩ አባላት ፍቃደኝነት እና ስምምነት በይፋ የተቋቋመ ሕዝባዊ ማሕበር (Civic Association) ነው። በተለያዩ ምክንያቶች ከአገር ቤት ለቀው እንዲሁም በኔዘርላንድ ተወልደው የሚኖሩ የአማራው ማሕበረሰብ በሚኖሩበት የኔዘርላንድ አገር ውስጥ ጠቃሚ ባህላቸውን እና ልምዶቻቸውን በፆታ፣ በዕምነት፣ በዕድሜ እና በፖለቲካ አመለካከት ላይ ልዩነት ሳያደርጉ በወንድምማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ ተሰባስበው ሳይለያዩ እርስ በርስ በመተሳሰብ የጋራ አቅማቸውን በማጎልበት ለመረዳዳት፣ በማንነትን ባህልን፣ የግል እና የገራ አቅምና ክህሎቶችን ለማዳበር ታስቦ የተመሠረተ ነው።
በኔዘርላንድ የሚገኙ ሁሉም የአማራ እና አማራ ወዳድ ወገኖችን በአንድ ጥላ ስር ተሳባስበው እና የእርስ በርስ ግንኙነታቸው ዳብሮ አማራውንም ሆነ ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፍ ሲታደጉ ማየት።
የማኅበሩን አባላት እና ደጋፊዎች በማሳደግ እና የማህበራዊ ግንኙነታቸውን በማጠናከር የአማራውን የህልውና ማዳንና ፍትህ ማስፈን ትግል በቀዳሚነት በመደገፍ አማራው በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆን እና መልሶ እንዲቋቋም በአንድነት ተሳትፎ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ማስቻል።